እንኳን ወደ ልደታ ክፍለ ከተማ
ህብረት ስራ ጽ/ቤት
የኦንላይን አገልግሎት
በደህና መጡ | Welcome
ጽ/ቤቱ የኅብረት ስራ ዕሴቶች፣ መርሆዎች፣
በሕብረተሰቡና በተቋማት እንዲታወቁ
ግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራትን ያከናወናል፡፡
የልደታ ክ/ከተማ ህብረት ስራ ጽ/ቤት
ጽ/ቤቱ በክ/ከተማችን የሚኖረው ህብረተሰብ
የአካባቢውን ሃብት መሰረት አድርጎ
ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሩን ለመፍታት ይሰራል!!
የልደታ ክ/ከተማ ህብረት ስራ ጽ/ቤት
ጽ/ቤቱ በገንዘብ ቁጠባና ብድር ማህበራት
የተደራጁትን አባላት የቁጠባ ባህል እንዲዳብር
የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል!
የልደታ ክ/ከተማ ህብረት ስራ ጽ/ቤት
የአባላትን ኑሮ መሻሻል በዘላቂነት ያረጋገጡና
በከተማው ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ የላቀ ሚና ያላቸው
ኅብረት ሥራ ማኅበራትን እንፈጥራለን!!

የልደታ ክፍለ ከተማ ህብረት ስራ ጽ/ቤት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙ መንግስታዊ ተቋማት ለተገልጋዩ ህብረተሰብ የሚሰጡ አገልግሎት ላይ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት ያለው የአሰራር ስርአትን በመዘርጋት ከተጠቃሚው ህብረተሰብ ጋር ስራን መሰረት ያደረገ ግንኑኝነት እንዲኖረ በማድረግ የለውጥ ስራወችን ህዝባዊ መስረት እንዲኖራቸው እየተደረገ ይገኛል ፡፡

ስለሆነም በልደታ ክ/ከተማ ህብረት ስራ ጽ/ቤት የሚሰጠው አገልግሎት የተገልጋይ ፍላጎትን ማዕከል አድርጎ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል የሚሰጡ አገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ስታንዳርድ፣ የሚሰጥበትን ቦታ እና ከተገልጋይ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በግልጽ በዝርዝር በማስቀመጥ የጽ/ቤቱ ሠራተኞች ዘመን የወለዳቸውን የቴክኖሎጂ ዉጤቶች አቀናጅቶ አገልግሎቶቹን በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሰረት ፍህታዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡና ተገልጋዮች ምን ዓይነት አገልግሎት በምን ዓይነት ደረጃ (standard) ማግኘት እንደሚገባቸው አውቀው በአገልግሎት አሠጣጥ ላይ የባለቤትነት ስሜት ተሰምቷቸው አስተያየት፤ ጥቆማና ግብዓት የሚሰጡበትን ሁኔታ ያመቻቸን መሆኑን በአክብሮት እናሳዉቃለን፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ
  • ራዕይ

    በ2022 ዓ.ም የአባላትንና ኑሮ መሻሻል በዘላቂነት ያረጋገጡና እና በከተማው ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ የላቀ ሚና ያላቸው ኅብረት ሥራ ማኅበራት ተፈጥረው ማየት፡፡

  • ተልእኮ

    በከተማችን የሚኖረው ህብረተሰብ የአካባቢውን ሃብት መሰረት አድርጎ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሩን ለመፍታት በፈቃደኝነት ላይ ተመስርቶ በተለያየ አይነትና ደረጃ የተደራጁ የኅብረት ስራ ማህበራትን መሰረተ ልማታቸውን በማጠናከር የግብይት ድርሻቸውን በማሳደግ፣ የአባላትን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ የህብረት ስራ ማህበራትን መፍጠር፡፡

  • እሴቶች (Values)

    ግልጽነት ፣ ተጠያቂነት ፣ ፍትሃዊነት እና አሳታፊነት ፣ ታማኝነት ፣ ቁርጠኝነት ፣ መተባበርና መቀናጀት ፣ በራስ መተማመን ፣ በህዝብ አገልጋይነት መኩራት ፣ ለአካባቢ እውቀት ክብር መስጠት ፣ ለስኬት እውቅና መስጠት ፣ በእኩልነት ማመን ፣ የማያቋርጥ የለውጥ ባህል ፣ በእውቀትና በእምነት መስራት

ቁጥራዊ መረጃዎች

CONTACT US

If you have any question please do not hesitate to call or contact us. Our Address is behind of Tesfakokeb School, Lideta Subcity Administration Buildindg 4th Floor, Addis Ababa.

Phone: +251118134145
Email: 2022

Get Direction
FIND US

© 2025 Lideta Cooperative Office. Designed by  Markos MG 0912689710.